ተግባርና ሀላፊነት
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን የሚረዱ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጅዎችንና መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀትና በመንግስት ሲፈቀዱም ተግባራዊ ማድረግ፣
 • ለኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ የገበያ እና ሌሎች መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ማደራጀትና እንደ አስፈላጊነቱ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣
 • ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለኬሚካልና ለኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት የሚያግዙና ዘርፉን ተወዳዳ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የስራ አመራርና ሌሎች እንደአስፈላጊነቱ የሚዘጋጁ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍን ለማሳደግ የሚያግዙ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ማከናወን፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ በአፈጻጸም ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ መስጠት፣ የኢንቨስትመንት ማነቆዎች እንዲወገዱ ድጋፍ መስጠትና ፕሮሞሽን ማካሄድ፣
 • በኬሚካልና በኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በቴክኖሎጂ መረጣ፣ በድርድር፣ በግንባታ፣ በተከላና በሙከራ ምርት የምክር ድጋፍ መስጠት፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ በምርት ሂደት፣ በምርት ዕቅድና በጥራት ቁጥጥር ላይ ድጋፍና የማማከር አገልግሎት መስጠት፣ የናሙና ምርት ማምረቻና ላቦራቶሪዎች በማቋቋም መደገፍ፣ ለሚያመርቷቸው ምርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፍተሻ አገልግሎት መስጠት፣ ኢንዱስትሪዎቹ የፍተሻ ላቦራቶሪዎች እንዲያቋቁሙ ማበረታታትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ማስቻል፣
 • በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቃትን ጠብቆ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እንዲችል በቁርኝት መርሃ ግብር አቅሙን መገንባት፣ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ከሚገኙ የግልና የመንግስት ተቋማት ጋር ትብር ማድረግና በግል ተቋማት መካከልም ተመሳሳይ ትብብር እንዲደረግ ማበረታታት፣
 • ከዩኒቨርስቲዎች ጋር የምርትና የሰው ኃይል ልማትን በተመለከተ በመተባበር መስራትና በጋራ የምርምር ስራዎችን ማካሄድ፣ ኢንዱስትሪው ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ትስስር እንዲኖረው ማገዝ፣ የኢንዱስትሪውን የዝቅተኛና መካከለኛ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማትን ሊያፋጥኑና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ የዓለም አቀፍ የምርጥ ተሞክሮዎች ጥናት ማካሄድና የሚቀመሩትን ተሞክሮዎች ተግባራዊ ለማድረግ ኢንዱስትሪዎቹ የሚደገፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
 • ለዘርፉ የግብዓቶች አቅርቦት በዓይነት በመጠንና በጥራት አስተማማኝ እንዲሆን የግብዓት ኢንዱስትሪው እንዲለማ መደገፍ፣ ከጥሬ ዕቃ አመራረት እሰከ ዓለም አቀፍ ገበያ ድረስ በምርቶች እሴት ሰንሰለት መሰረት በዘርፉ ተዋናዮች መካከል ያለው ትስስር ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ በተለይም በዘርፉ የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ አምራቾች ኢንዱስትሪው ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ጋር ውጤታማ የምርት፣ የቴክኖሎጂና የስልጠና ትስስር እንዲኖራቸው መደገፍ፣
 • የአገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች በዘርፉ ላይ ለመሰማራት እንዲነሳሱ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ቀጣናዎች እንዲለሙ ማበረታታት፣ በኢንዱስትሪ ቀጣናዎቹ ውስጥ የሚሰሩ ባለሀብቶችን መደገፍ፣
 • በዘርፉ ተዋናዮች የሚገኙ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት እንዲጠበቅላቸው ድጋፍ መስጠት፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ታዳሽ የሀይል ምንጮችን እንዲጠቀም እና የአካባቢ ብክለት እንዳያስከትል ድጋፍ መስጠት፣
 • የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ማህበራት ለዘርፉ ንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ የአቅም ግንባታ ድጋፎችን መስጠት፣
 • ከኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ስምምነት አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ከአባልነት የሚገኙ የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፎችን ለኬሚካል ኢንዱስትሪው ልማት አቅም ግንባታ መጠቀም፣
 • የግብዓትና የምርት ትስስር እንዲፈጠር ድጋፍ መስጠት፣
 • ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በመንግስት በሚወሰን ተመን መሰረት የአገልግሎት ዋጋ የማስከፈል፣
 • የንብረት ባለቤት መሆን፣ ውል መዋዋል፣በራሱ ስም መክሰስና መከሰስ፣
 • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ማከናወን ናቸው፡፡