ተግባርና ሀላፊነት
 • የምግብ፣ የመጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን የሚረዱ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀትና በመንግስት ሲፈቀዱም ተግባራዊ ማድረግ፣
 • በምግብ፣ በመጠጥና በፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ሊለሙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በምርምርና ስርፀት መለየት፣ በባህላዊ ምርቶች ላይና በአዳዲስ ምርቶች ላይ የምርት ሂደትና የምርት ልማት ስራ ማከናወንና እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢንዱስትሪው በማሸጋገር ወደ ገበያ እንዲገቡ መደገፍ፤ ኢንዱስትሪው የምርምርና ስርፀት ክፍሎች እንዲያቋቁም መደገፍ፣
 • የምግብ፣ የመጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ለማሳደግ የሚያግዙ የገበያ ጥናትን ጨምሮ ሌሎች የጥናትና ምርምር ስራዎች ውስጥ እንዲሁም በዓለም ገበያ ለማስተዋወቅ ድጋፍ መስጠት፤ ውጤታማ የግብይት ስርዓት እንዲዘረጋ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትጋር በቅንጅት መስራት፣
 • ለምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ የገበያና ሌሎች መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ማደራጀትና እንደ አስፈላጊነቱ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣
 • የምግብ፣ የመጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ በፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ ለሚከሰቱት ችግሮች መፍትሔ መስጠት፣ የኢንቨስትመንት ማነቆዎች እንዲወገዱ ድጋፍ ማሰጠትና ፕሮሞሽን ማካሄድ፣
 • በምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በቴክኖሎጂ መረጣ፣ በድርድር፣ በግንባታ፣ በተከላና በሙከራ ምርት የምክር ድጋፍ መስጠት፣
 • ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር፣ የምግብ፣ የመጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማትን የሚያግዙና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የስራ አመራርና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፣
 • ለምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ በምርት ሂደት፣ በምርት ዕቅድና በጥራት ቁጥጥር ላይ ድጋፍና የማማከር አገልግሎት መስጠት፣ የናሙና ምርት ማምረቻና ላብራቶሪዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፍተሻ አገልግሎት መስጠት፣ ኢንዱስትሪው የፍተሻ ላቦራቶሪዎች እንዲያቋቁም ማበረታታትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ሰርተፍኬሽን እንዲያገኙ ማስቻል፣
 • በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቃትን ጠብቆ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እንዲችል በቁርኝት መርሀ ግብር አቅሙን መገንባት፣ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ የግልና የመንግስት ተቋማት ጋር ትብብር ማድረግና በግል ተቋማት መካከልም ተመሳሳይ ትብብር እንዲደረግ ማበረታታት፤
 • ከዩኒቨርስቲዎች ጋር የምርትና የሰው ኃይል ልማትን በተመለከተ በመተባበር መስራትና በጋራ የምርምር ስራዎችን ማካሄድ ኢንዱስትሪው ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ትስስር እንዲኖረው ማገዝ፤ የኢንዱስትሪውን የዝቅተኛና መካከለኛ የሰው ኃይል ፍላጐት ለማሟላት ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት፤
 • የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማትን ሊያፋጥኑና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ የዓለም አቀፍ የምርጥ ተሞክሮዎች ጥናት ማካሄድና የሚቀመሩትን ተሞክሮዎች ተግባራዊ ለማድረግ ለኢንዱስትሪው ድጋፍ መስጠት፣
 • ለዘርፉ የግብዓቶች አቅርቦት በዓይነት፣ በመጠንና በጥራት አስተማማኝ እንዲሆን የግብይት ኢንዱስትሪው እንዲለማ መደገፍ ከጥሬ እቃ አመራረት እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ ድረስ በምርቶች እሴት ሰንሰለት መሰረት ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤ በተለይም በዘርፉ የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ኢንዱስትሪው ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪው ጋር ውጤታማ የምርት፣ የቴክኖሎጂና የስልጠና ትስስር እንዲኖረው መደገፍ፣
 • የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በዘርፉ ላይ ለመሰማራት እንዲነሳሱ የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ቀጠናዎች እንዲለሙ ማበረታታት፣ በኢንዱስትሪ ቀጠናዎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሀብቶችን መደገፍ፤
 • በዘርፉ አዳዲስና ተወዳዳሪ ባለሀብቶችን ለመፍጠር የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ፕሮግራም መዘርጋትና የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማቋቋም፤
 • የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪው በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን የማሸጊያ ምርቶች ኢንዱስትሪ ልማትን መደገፍ፤
 • በዘርፉ ተዋናዮች የሚገኙ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት እንዲጠበቅላቸው ድጋፍ መስጠት፣
 • የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ታዳሽ የኃይል ምንጮችን እንዲጠቀምና የአካባቢ ብክለት እንዲያስከትል ድጋፍ መስጠት፣
 • የባዮ-ኢኩቫለንስ ማዕከል በማጠናከር በኢትዮጵያ ያሉት የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • በድህረ - ምርት የሚያጋጥሙ የምርት ብክነቶችን ለመቀነስ ድህረ - ምርት ቴክኖሎጂዎች፣ የማቀዝቀዣ ሰንሰለቶች ዘመናዊ መጋዘኖች፣ ዘመናዊ ትራንስፖርትና ሌሎች አስፈላጊ የሎጂስቲክስ መሰረተ ልማቶች እንዲስፋፉ መደገፍ፣
 • የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ማህበራት ለዘርፉ ንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ የአቅም ግንባታ ድጋፎች ማሰጠት፣
 • የንብረት ባለቤት መሆን፣ ውል መዋዋል፣ በራሱ ስም መክሰስና መከሰስ፣
 • ለሚመለከታቸው አገልግሎቶች በመንግስት በሚተመን መሰረት የአገልግሎት ዋጋ ማስከፈል፣
 • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ማከናወን፡፡